በክልሉ የሚገኙ የተፈጥሮ ፀጋዎችን በማልማት የዜጎችን ሁለንተናዊ ብልጽግና ማረጋገጥ ይገባል - ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን - ኢዜአ አማርኛ
በክልሉ የሚገኙ የተፈጥሮ ፀጋዎችን በማልማት የዜጎችን ሁለንተናዊ ብልጽግና ማረጋገጥ ይገባል - ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን
አሶሳ፤ ህዳር 3/2018(ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኙ የተፈጥሮ ፀጋዎችን በማልማት የዜጎችን ሁለንተናዊ ብልጽግና ማረጋገጥ እንደሚገባ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን ገለጹ።
ርዕሰ መስተዳድሩ የክልል፣ የዞን፣ የወረዳ እና የከተማ አስተዳደር አመራሮች በተገኙበት የክልሉን ፀጋዎች አልምቶ መጠቀም በሚቻልበት መንገድ ላይ የውይይት መድረክ አካሂደዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ በመድረኩ ላይ ባቀረቡት የመወያያ ሰነድ በክልሉ የአካባቢውን ፀጋዎችን በማልማት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማሳደግ እየተሰራ ነው ብለዋል።
በክልሉ ገቢዎችን አሟጦ በመሰብሰብ የራስን ወጪ በራስ አቅም በመሸፈን ትላልቅ የልማት ፕሮጀክቶችን ማከናወን ዋነኛው የትኩረት አቅጣጫ መሆኑን ገልጸዋል።
በክልሉ የሚገኙ የተፈጥሮ ፀጋዎችን በማልማት የተጀመሩ ስራዎችን በማጠናከር የክልሉን ኢኮኖሚ ማሳደግ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
ከለውጡ ወዲህ በግብርና፣ በማዕድንና ሌሎች ዘርፎች በክልሉ የተገኙ ውጤቶችን በተቀናጀ መልኩ ማስቀጠል ይገባል ያሉት አቶ አሻድሊ፤ በዚህ ረገድ አመራሩ በላቀ ቁርጠኝነት ሊሰራ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
በክልሉ የተጀመሩ የኮሪደር ልማት ስራዎችን ማስፋት፤ ጠንካራ ተቋማት ግንባታ እና መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ማዕከልን አጠናክሮ በመቀጠል የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማሳደግ እንደሚገባም አሳስበዋል።