በየደረጃው የሚገኙ የክልሉ አመራሮች በፈጠራና ፍጥነት ለላቀ አፈፃፀም ዝግጁ ሊሆኑ ይገባል- ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) - ኢዜአ አማርኛ
በየደረጃው የሚገኙ የክልሉ አመራሮች በፈጠራና ፍጥነት ለላቀ አፈፃፀም ዝግጁ ሊሆኑ ይገባል- ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)
ቦንጋ፤ ህዳር 03/2018(ኢዜአ)፦ በየደረጃው የሚገኙ የክልሉ አመራሮች በፈጠራና ፍጥነት ለላቀ አፈፃፀም ዝግጁ ሊሆኑ እንደሚገባ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
በክልሉ በበጀት ዓመቱ በልዩ ትኩረትና ንቅናቄ በሚከናወኑ ተግባራት ላይ በማተኮር የክልሉ አመራሮች የውይይት መድረክ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ነው።
በመድረኩ ላይ የተገኙት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በየደረጃው የሚገኙ የክልሉ አመራሮች በፈጠራና ፍጥነት ለላቀ አፈፃፀም ዝግጁ መሆን እንዳለባቸው አሳስበዋል።
የተጀመሩ እና በእቅድ የተያዙ የልማት ስራዎችን ለማሳካት መትጋት፣ ለውጤት ማብቃትና ማሳካት ያስፈልጋል ሲሉም አስገንዝበዋል።
ለዚህም በየደረጃው ያሉ አመራሮች ቁርጠኝነት፣ የመፈፀም አቅምና ለህዝብ አገልግሎት የላቀ ዝግጁነት ሊኖራቸው እንደሚገባ አፅዕኖት ሰጥተዋል።
በክልሉ የተጀመሩ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎችን ለማሳካትና የህዝቡን የልማትና የአገልግሎት ፍላጎቶች መሰረት አድርጎ ምላሽ ለመስጠት የተቀናጀ ጥረትና የስራ ትጋት አስፈላጊ መሆኑን አንስተዋል።
የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግር ለማምጣት በመንግሥት የተቀመጡ አቅጣጫዎችን በመከተል መተግበር የግድ መሆኑንም አስገንዝበዋል።
በየደረጃው የሚገኙ የክልሉ አመራሮች በፈጠራና ፍጥነት ለላቀ አፈፃፀም ዝግጁ ሊሆኑ ይገባል በማለትም አሳስበዋል።
በተለይም በግብርናው፣ በኢንዱስትሪ እና በቱሪዝም ዘርፎች በክልሉ ያሉ እምቅ ሃብቶችን አሰናስሎ በማልማት ምርታማነትን ማሳደግ አስፈላጊ መሆኑን ርእሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል።
በመድረኩ የክልል፣ የዞንና የወረዳ እንዲሁም የከተማ አስተዳደር አመራሮች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።