የታሪክ ተመራማሪው ላጲሶ ጌ’ዴሌቦ (ፕ/ር) የአስከሬን ሽኝት ሥነ -ሥርዓት እየተካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የታሪክ ተመራማሪው ላጲሶ ጌ’ዴሌቦ (ፕ/ር) የአስከሬን ሽኝት ሥነ -ሥርዓት እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፤ሕዳር 2/2018 (ኢዜአ)፡-የላጲሶ ጌ’ዴሌቦ (ፕ/ር) አስከሬን ሽኝት መርሐ ግብር በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 6 ኪሎ ካምፓስ እየተካሄደ ነው፡፡
በሽኝት ሥነ-ሥርዓቱ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት፣ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች የፕሮፌሰሩ የሥራ ባልደረቦችና ወዳጅ ዘመዶች ተገኝተዋል።
የታሪክ ተመራማሪው ላጲሶ ጌ’ዴሌቦ (ፕ/ር) ባደረባቸው ሕመም ሕክምናቸውን ሲከታተሉ ቆይተው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ይታወቃል፡፡
ፕሮፌሰር ላጲሶ በኢትዮጵያና በአፍሪካ የታሪክ ጥናትና ምርምር በማካሄድ የተለያዩ የታሪክ መጽሐፍትን ለአንባቢያን በማበርከት አገራቸውን አገልግለዋል፡፡