ቀጥታ፡

ሊቨርፑል ወደ አሸናፊነት ተመልሷል

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 22/2018 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ10ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ሊቨርፑል አስቶንቪላን 2 ለ 0 አሸንፏል።

ማምሻውን በአንፊልድ ሮድ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ መሐመድ ሳላህ እና ራያን ግራቫንበርች ግቦቹን አስቆጥረዋል።

ሳላህ በሊቨርፑል ማልያ 250ኛ ግቡን ከመረብ ላይ አሳርፏል። በክለቡ የምንጊዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት ዝርዝር ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ውጤቱን ተከትሎ ሊቨርፑል ከአራት ተከታታይ ሽንፈት በኋላ ወደ አሸናፊነት ተመልሷል። ቡድኑ በጨዋታው የተሻለ እንቅስቃሴ አሳይቷል።

ቀያዮቹ በሊጉ ስድስተኛ ድላቸውን በማስመዝገብ በ18 ነጥብ ደረጃቸውን ወደ ሶስተኛ ከፍ አድርገዋል።

በሊጉ ሶስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው አስቶንቪላ በ15 ነጥብ 11ኛ ደረጃን ይዟል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም