ቼልሲ ቶተንሃም ሆትስፐርስን አሸነፈ - ኢዜአ አማርኛ
ቼልሲ ቶተንሃም ሆትስፐርስን አሸነፈ
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 22/2018 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ10ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ቼልሲ ቶተንሃም ሆትስፐርስን አሸንፏል።
ማምሻውን በቶተንሃም ሆትስፐርስ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ጆአኦ ፔድሮ በ34ኛው ደቂቃ ላይ የማሸነፊያውን ግብ አስቆጥሯል።
ውጤቱን ተከትሎ ቼልሲ በሊጉ አምስተኛ ድሉን በማስመዝገብ በ17 ነጥብ ደረጃውን ወደ አራተኛ ከፍ አድርጓል።
በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ ሶስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ቶተንሃም ሆትስፐርስ በተመሳሳይ 17 ነጥብ በግብ ክፍያ በልጦ ሶስተኛ ደረጃን ይዟል።