የሊጉ መሪ አርሰናል ድል ሲቀናው ማንችስተር ዩናይትድ አቻ ወጥቷል - ኢዜአ አማርኛ
የሊጉ መሪ አርሰናል ድል ሲቀናው ማንችስተር ዩናይትድ አቻ ወጥቷል
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 22/2018 (ኢዜአ):- በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ10ኛ ሳምንት መርሃ ግብር አርሰናል በርንሌይን 2 ለ 0 አሸንፏል።
በተርፍ ሙር ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ቪክቶር ዮኮሬሽ እና ዴክላን ራይስ ግቦቹን መከረብ ላይ አሳርፈዋል።
በሊጉ ስምንተኛ ድሉን ያስመዘገበው አርሰናል በ25 ነጥብ መሪነቱን አጠናክሯል።
በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ ስድስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው በርንሌይ በ10 ነጥብ 17ኛ ደረጃን ይዟል።
በሌላኛው መርሃ ግብር ማንችስተር ዩናይትድ ከኖቲንግሃም ፎረስት ሁለት አቻ ተለያይተዋል።
ካሲሚሮ እና አማድ ዲያሎ ለማንችስተር ዩናይትድ ግቦቹን አስቆጥረዋል። ሞራጋን ጊብስ-ዋይት እና ኒኮሎ ሳቮና ብቸኛውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
ማንችስተር ዩናይትድ ከሶስት ተከታታይ ጨዋታዎች ድል በኋላ አቻ በመውጣት በ17 ነጥብ አምስተኛ ደረጃን ይዟል።
ኖቲንግሃም ፎረስት በስድስት ነጥብ 18ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።
በሌሎች ጨዋታዎች ብራይተን ሊድስ ዩናይትድን እና ፉልሃም ዎልቭስን በተመሳሳይ 3 ለ 0 ሲያሸንፉ ክሪስታል ፓላስ ብሬንትፎርድን 2 ለ 0 ረቷል።