በብዝኃነት የደመቀውና የልማት አርበኛ የሆነው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ የህዳሴን ድል በሌሎች ልማቶች ለመድገም ተነስቷል - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ - ኢዜአ አማርኛ
በብዝኃነት የደመቀውና የልማት አርበኛ የሆነው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ የህዳሴን ድል በሌሎች ልማቶች ለመድገም ተነስቷል - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 8/2018(ኢዜአ)፦ በብዝኃነት የደመቀውና የልማት አርበኛ የሆነው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ የህዳሴን ድል በሌሎች ልማቶች ለመድገም ተነስቷል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።
ተባብሮ፣ በጋራ ተመካክሮ መልማትን እንደ እጁ መዳፍ ጠንቅቆ የሚያውቀው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሕዝብ፤ በህዳሴ ግድብ መጠናቀቅ የድጋፍ ሰልፍ ያስተጋባቸው መልዕክቶች የእስከዛሬ ስኬቶቻችን ሳያዘናጉን ለተሻለው እንድንበረታ ጉልበት የሚሰጠን የሰላም እና የልማት ሰልፍ ነው ሲሉም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠቁመዋል።
ዛሬ በክልሉ የታየው ልማትን አጀንዳ ያደረገ ሰልፍ የማንሠራራት ዘመናችን መሰረት እንደያዘ ማሳያ ነው ሲሉም ገልጸዋል፡፡
የተስተጋቡት መፈክሮችም ሕዝቡ ለመንግስት የሰጣቸው የልማት አደራዎች ጭምር እንደሆኑ ተገንዝበናል ነው ያሉት በመልዕክታቸው፡፡