የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ ተጀመረ

ጋምቤላ፤መጋቢት 15/2017 ( ኢዜአ)፡-የጋምቤላ ሕዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት 6ኛ የምርጫ ጊዜ 4ኛ የስራ ዘመን 7ኛ መደበኛ ጉባኤ ዛሬ በጋምቤላ ከተማ መካሄድ ጀመረ።

ጉባኤው ዛሬን ጨምሮ በሚኖረው የሶስት ቀናት ቆይታ የክልሉን የ2017 የግማሽ በጀት ዓመት የልማትና የመልካም አስተዳድር፣የኦዲት፣ የጠቅላይ ፍርድ ቤት እቅድ ክንውን ሪፖርት ማድመጥ እና ውይይት ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።

እንዲሁም የክልሉን የቀጣይ ግማሽ የበጀት ዓመት የተከለሰ የልማትና የመልካም አስተዳደር፣ የኦዲት፣ የጠቅላይ ፍርድ ቤት እቅድ፣የተለያዩ ረቂቅ አዋጆችና ሌሎች ጉዳዮች ላይ ውይይት በማድረግ ውሳኔ እንደሚሳልፍም እንዲሁ።

በጉባኤው ላይ የምክር ቤት አባላትን ጨምሮ የክልል፣ የዞን፣ የወረዳ አመራር አባላት፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የኃይማኖት አባቶችና ሌሎች ተጋባዥ እንገዶች በመሳተፍ ላይ ናቸው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም