ቀጥታ፡

የቴአትርና የፊልም ባለሙያው ኩራባቸው ደነቀ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 20/2016 (ኢዜአ)፡-የቴአትርና የፊልም ባለሙያው ኩራባቸው ደነቀ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

አርቲስት ኩራባቸው ደነቀ የተወለደው በ1957 ዓ.ም በሐረር ከተማ ነው።

ኩራባቸው በ1979 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በቴአትር ትምህርት የመጀመሪያ ዲግሪውን አግኝቷል።

ባለፉት 35 አመታት በትወና፣ የመድረክ ቴአትሮችና የቴሌቪዥን ድራማዎች ላይ በመሳተፍ ሙያዊ አስተዋጽኦ አድርጓል።

አርቲስቱ ባለትዳርና የሁለት ወንዶችና የአንድ ሴት ልጅ አባት ነበር።

የኩራባቸው የቀብር ስነ ስርዓት ነገ ነሐሴ 21 ቀን 2016 ዓ.ም በቀጨኔ መድሃኒዓለም ቤተክርስቲያን ይፈጸማል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም