የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን የግንባታ ጥበብ የሚያስቃኝ ቋሚ አውደ ርዕይ በላሊበላ ከተማ ተከፈተ 

182

አዲስ አበባ ግንቦት 26/2015 (ኢዜአ)፡- የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን የግንባታ ጥበብ ከውጥን እስከ ፍፃሜ የሚያስቃኝ ቋሚ አውደ ርዕይ በላሊበላ ከተማ ዛሬ ተከፍቷል። 

ቋሚ አውደ ርዕዩ በፈረንሳይ ልማት ኤጀንሲ ድጋፍ በትግበራ ላይ በሚገኘው 'የዘላቂ ላሊበላ ልማት ፕሮጀክት' አካል ነው። 

የአውደ ርዕዩ መክፈቻ ስነ ስርዓት ላይ የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ስለሺ ግርማን ጨምሮ ከፍተኛ የፌዴራልና የክልል የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የፈረንሳይ ኤምባሲና የፈረንሳይ ልማት ኤጀንሲ ተወካዮች እና የአካባቢው ማህበረሰብ ተገኝተዋል።

በፈረንሳይ መንግስት ድጋፍ የላሊበላ ታሪካዊ ቅርሶች ጥገና እና የላሊበላ ከተማን የቅርስ ልማት የሚያከናውነው የአምስት ዓመቱ 'የዘላቂ ላሊበላ ፕሮጀክት' ተግባራዊ በመሆን ላይ ይገኛል።

'ላሊበላ በእምነት የታነፀ' በሚል መሪ ሀሳብ የተዘጋጀው አውደ ርዕይ የላሊበላ ጎብኝዎችን ቆይታ ለማራዘም ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ተገልጿል።

በተመሳሳይ ከዚህ በፊት ከመስከረም 26 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በእንጦጦ ፓርክ የላሊበላ ቅርሶችን የሚዘክር አውደ ርዕይ ለሁለት ወራት ለሕዝብ ክፍት ሆኖ መቆየቱ ይታወሳል።

በወቅቱም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የመንግስት አመራሮችና የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች አውደ ርዕዩን መጎብኘታቸው ይታወቃል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም