የፌዴራል ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች በወቅታዊ ሀገራዊ የሰላም፣የፀጥታና የልማት ጉዳዮች ላይ ውይይት እያደረጉ ነው

525


አዲስ አበባ መጋቢት 15/2015(ኢዜአ)፦የፌዴራል ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች በወቅታዊ ሀገራዊ የሰላም፣የፀጥታ እና የልማት ጉዳዮች ላይ የሚያደርጉትን ውይይት በዛሬው እለት ጀምረዋል። 

"የውይይት መድረኩ ተቋማዊ አቅምን በመገንባት ስኬቶቻችንን እናጠናክራለን" በሚል መሪ ቃል የሚካሄድ ሲሆን እንደ ሀገር ያገኘናቸውን ስኬቶች አጠናክረን ለመቀጠል እንዲሁም ለሚስተዋሉ ችግሮች እልባት ለመስጠት አቅጣጫ የሚቀመጥበት ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።


 


የአመለካከትና የተግባር አንድነትን በማጠናከር በተሰናሰለ ህብረ ብሔራዊ እሳቤ በመመራት የሚያጋጥሙ ፈተናዎችን በርብርብ በመፍታት የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልፅግና እውን ለማድረግ መትጋት እንደሚያስፈልግም በመድረኩ ተጠቅሷል። 



አመራሩ ድሎችን የማፅናትና ፈተናዎችን የመሻገር ታሪካዊ ተልእኮ ተቀብሎ በመሰማራት ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልፅግና የሚጠበቅበትን በጎ አሻራ እንዲያስቀምጥ ብሎም ውስጣዊ አንድነቱን በማጠናከር ፈተናዎችን በድል የመሻገር አቅም የሚያዳብርበት መድረክ ይሆናል። 


መድረኩ ለተከታታይ 3 ቀናት የሚቀጥል ሲሆን በርካታ ሰነዶች ቀርበው ውይይት የሚደረግባቸው መሆኑን ከብልጽግና ፓርቲ ማህበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም