በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከተጻፈው የመደመር ትውልድ መጽሐፍ የሚገኘው ገቢ ለቱሪዝም መስህብ ስፍራ ማሻሻያ ይውላል--የሃረሪ ክልል

582

አዲስ አበባ መጋቢት 10/2015(ኢዜአ)፦በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከተጻፈው የመደመር ትውልድ መጽሐፍ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በክልሉ ለቱሪዝም መስህብ ስፍራ ማሻሻያ እንደሚውል የሃረሪ ክልል አስታወቀ።


 

በኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተፃፈው የ"መደመር ትዉልድ" መፅሐፍ በትላንትናው እለት መመረቁ ይታወቃል።


 

ይሄንን ተከትሎም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በገቡት ቃል መሰረት በክልሉ ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘውን ገቢ የቱሪስት አገልግሎቱ ይበልጥ ምቹ እንዲሆን የጅብ ማብላት ትርኢት ማሳያ ስፍራውን ለማሻሻል እንደሚውል የክልሉ ኮሙኒኬሽን በማህበራዊ ትስስር ገጹ ያሰፈረው መረጃ ያመለክታል።


 

ይሄንን እድል ላመቻቹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ምስጋናውን በማቅረብም በክልሉ የሚገኙ ነዋሪዎች ፣ ባለሀብቶች፣ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የ'መደመር ትዉልድ' መጽሐፍን በመግዛት የቱሪዝም እንቅስቃሴውን ለማሳደግ በሚደረገው ጥረት የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርቧል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም