በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ከመሬት ምዝበራ ጋር በተያያዘ 2 አመራሮችና 6 ባለሙያዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ - ኢዜአ አማርኛ
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ከመሬት ምዝበራ ጋር በተያያዘ 2 አመራሮችና 6 ባለሙያዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
አዲስ አበባ (ኢዜአ) ጥር 8/2015 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ከመሬት ምዝበራ ጋር በተያያዘ ሁለት አመራሮችና ስድስት ባለሙያዎች በጥቅሉ ስምንት በሙስና የተጠረጠሩ አመራሮችና ባለሙያዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡
አመራሮች
1. አቶ መለሰ ጋሻው የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ሃላፊ
2. አቶ ፍቃዱ መለሰ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ የመሬት ማኔጅመንት ፅህፈት ቤት ሃላፊ ሲሆኑ
ፈፃሚዎች
3. አቶ ሄኖክ ፍቃዱ (የመሬት አገልግሎት መሻሻያ ዘርፍ አስተባባሪ)
4. ሜሮን ማህረይ (የቤዝ ማፕ ባለሙያ)
5. አቶ በላይህ ተፈሪ (የቤዝ ማፕ ባለሙያ)
6. አቶ ፍቅሬ ብርሃኑ (ፋይል አደራጅ)
7. ወ/ሮ ዘላለም በዛብህ (የሲአይ ኤስ ባለሙያ)
8. አቶ ሃጎስ በርሄ (የሰነድ አጣሪ ባለሙያ) ናቸው፡፡
የተጀመረው ህግን የማስከበር ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የአዲስ አበባ ከተማ የፀረ ሙስና ኮሚቴ ማስታወቁን የከንቲባ ጽህፈት ቤት መረጃ ጠቁሟል፡፡