ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ሱዳን ገቡ

93

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 19/2012( ኢዜአ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ሱዳን ካርቱም ገቡ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ሱዳን ሲደርሱ የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክና የአገሪቱ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሱዳን በሚኖራቸው ቆይታ ከአገሪቱ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር ተገኛኝተው የሁለትዮሽ ግንኙነት በሚጠናከርበትና በሌሎች ቀጣናዊና ዓለም ዓቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል። 

በሱዳን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ልዩ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ ትናንት የሹመት ደብዳቤያቸውን ለሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ለሌትናንት ጄኔራል አብዱልፈታ አልቡርሃን ማቅረባቸው ይታወሳል።

በዚሁ ወቅት ሌትናንት ጄኔራል አብዱልፈታ አልቡርሃን የሁለቱን አገሮች ሁለገብ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር መስራት እንደሚገባ ገልጸው፤ የአምባሳደሩ የሱዳን ቆይታና ሥራ የተሳካ እንዲሆን መንግስታቸው አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግላቸው አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም