በኢትዮጵያ ተጨማሪ 1 ሺህ 638 ሰዎች ኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው፤ የ16 ሰዎች ሕይወት አልፏል

53

ነሐሴ 17/2012(ኢዜአ) ባለፉት 24 ሰዓታት በኢትዮጵያ በተደረገው 20 ሺህ 153 የላቦራቶሪ ምርመራ 1 ሺህ 638 ሰዎች ኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

በዚህም በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 40ሺህ 671 ደርሷል፡፡

የተጨማሪ 16 ሰዎች ሕይወት ያለፈ ሲሆን ፤በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 678 መድረሱ ታውቋል።

በአሁኑ ወቅት 291ሰዎች በጽኑ ሕክምና ላይ የሚገኙ ሲሆን፤ 24ሺህ 996 ደግሞ ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች ቁጥር እንደሆነ ተገልጿል።

በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት 515 ሰዎች ከቫይረሱ ያገገሙ ሲሆን፤ በአጠቃላይ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 14ሺህ 995 ደርሷል፡፡

በኢትዮጵያ በአጠቃላይ እስካዛሬ ድረስ 757 ሺህ 57 የላቦራቶሪ ምርመራ ተከናውኗል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም