በኬኒያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በኮሮና ወረርሽኝ ዜጎች እንዳይጎዱ ድጋፍ ላደረጉ ምሥጋና አቀረበ

71

ነሃሴ 15/2012 (ኢዜአ) በኬኒያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ዜጎች በኮሮና ቫይረስ እንዳይጎዱ ለመርዳት ላስተላለፈው ጥሪ ድጋፋቸውን ላደረጉ የኮሚኒቲ አባላትና ለዓለም አቀፍ የፍልሰት ድርጅት ምሥጋና አቀረበ።

ኤምባሲው ባቀረበው ጥሪ መሠረት ከ53 ሺህ በላይ የአሜሪካን ዶላርና ከ700 ሺህ በላይ የኬኒያ ሽልንግ በሁለት ዙር የኮሚኒቲ አባላት መለገሳቸውን አስታውሷል።

ገንዘቡም ወደ ሀገር ቤት በመላክ በወረርሽኙ ምክንያት ከሥራቸው የተናፈቀሉና ችግር የደረሰባቸው ዜጎችን በመርዳት አስተዋጽኦ ማበርከት መቻላቸውን ኤምባሲው አመልክቷል፡፡

በናይሮቢ የኢፌዲሪ. ኤምባሲ ለዓለም አቀፍ የፍልሰት ድርጅት (IOM) ዕርዳታ በመጠየቅ በሁለት ዙር 490 ቤተሰቦች ለአንድ ወር የሚሆን ቀለብና የጽዳት ዕቃዎች መርዳት መቻሉን ገልጿል፡፡

ለሦስተኛ ዙርም ድርጅቱ ለመርዳት በመስማማቱ 390 ቤተሰቦች ዝርዝር ለድርጅቱ ማስተላለፉን ኤምባሲው አስታውቋል።

ኤምባሲው አያይዞም ድርጅቱ በቅርቡ ዕርዳታውን ለኤምባሲው እንደሚያስረክብም ይጠበቃል ብሏል፡፡

ኤምባሲውና የኮሚቴ አባላት ለኮሚኒቲውና ለዓለም አቀፍ የፍልሰት ድርጅት (IOM) ላደረጉት ዕርዳታ ላቅ ያለ ምሥጋና ማቅረባቸውን አመልክቷል፡፡

ኤምባሲው አያይዞም “የኢትዮጵያ ኤምባሲና የኮሚኒቲ አባላት ለወገን ደራሽ ወገን መሆኑን ያረጋገጡ በመሆኑ ዕርዳታው በተደረገላቸው ወገኖቻችን ሥም የላቀ ምሥጋና ማቅረብ ይወዳል” ብሏል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም