የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ በኢትዮጵያ የሱዳኑን አምባሳደር የሹመት ደብዳቤ ተቀበሉ

117

አዲስ አበባ፤ ነሀሴ 7/2012 (ኢዜአ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው በኢትዮጵያ የሱዳን አምባሳደር በመሆን የተሾሙትን ጀማል ኢል ሸኪ የሹመት ደብዳቤ ተቀበሉ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር  በዚህ ወቅት እንደተናገሩት የሁለቱ አገራት ግንኙነት ዘመናትን ያስቆጠረና በብዙ መልኩ በሚገለጽ ወንድማማችነትና ወዳጀነት ላይ የተመሰረተ ነው።

ኢትዮጵያ የሁለቱን አገራት ዘላቂ ጥቅምና ፍላጎት ባስጠበቀ መልኩ ለዘመናት የቆየውን ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ትሰራለችም ብለዋል።

የሱዳኑ አምባሳደር በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ ለሥራቸው መቃናት አስፈላጊው ድጋፍ ይደረግላቸዋልም ብለዋል። 

የሱዳኑ አምባሳደር ጀማል ኢል ሸኪ በበኩላቸው በኢትዮጵያ ለሁለተኛ ግዜ ተሹመው መምጣታቸውን በማስታወስ፤ የረጅም ዘመናት የባህል፣ የታሪክና የአስተሳሰብ ትስስር ያላቸውን ወንድማማች ህዝቦች በአምባሳደርነት ለማገልገል በመምጣታቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል።

በቆይታቸውም የሁሉቱን አገራት ግንኙነት በሁሉም ዘርፍ ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት በማከው መግለጫ አመልክቷል።።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም