የአማራ ብልፅግና ፓርቲ ኮንፈረንስ በባህር ዳር ተጀመረ

95

ባህር ዳር፣ ነሐሴ 4/2012 (ኢዜአ) የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ በክልላዊና ሀገራዊ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለመምከር ዛሬ በባህር ዳር ከተማ ኮንፈረንስ ማካሄድ ጀመረ።

የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች የተሳተፉበት ኮንፈረንስ ለሁለት ቀን እንደሚቆይ ተነግሯል።

አመራሮቹ በክልሉና በሀገሪቱ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በመምከር የቀጣይ አቅጣጫ ያስቀምጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በተለይም ለውጡን ከግብ ለማድረስ እየተሰሩ ባሉ ተግባራት፣ ሊዳብሩ በሚችሉ ውጤቶችና  በሂደቱ ያጋጠሙ መሰናክሎችን በመለየት ዘላቂ የመፍትሄ እርምጃዎችን እንደሚያስቀምጡ ከመርሀ ግብሩ ለመረዳት ተችሏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም