ዩኒሴፍ ከ700 ሺህ ብር በላይ ግምት ያላቸው የኮሮና መከላከያ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረገ

53

መቀሌ፣ ነሐሴ 1/2012(ኢዜአ ) በተባበሩት መንግስታት የህጻን መርጃ ድርጅት /ዩኒሴፍ/ በትግራይ ክልል ከ700 ሺህ ብር በላይ ግምት ያላቸው የኮሮና መከላከያ ቁሳቁሶች ዛሬ ድጋፍ አደረገ።

ድርጅቱ  ያደረገው ድጋፍ   በክልሉ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ አማካኝነት   በትግራይ በሴፍትኔት ፕሮግራም ለታቀፉ ወገኖች ነው።

የክልሉ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ወይዘሮ ንግስቲ ወልደሩፋኤል  ድጋፉን  ለማህበረሰብ ተወካዮች አስረክበዋል።

ወይዘሮ ንግስቲ  በዚህ ወቅት  እንደተናገሩት ዩኒሴፍ ያደረገው ድጋፍ ከ715 ሺህ ብር በላይ ግምት ያላቸው  የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል የሚያግዙ ቁሳቁሶች ናቸው።

ድጋፍ ሳንታይዘር ፣ አልኮል ፣  ሳሙና፣  የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ያካተተ ነው።

ይህም  በሴፍትኔት ፕሮግራም ለታቀፉ 2ሺ 398 የመቀሌና ዘላአምበሳ ከተማ ነዋሪዎች በተወካዮቻቸው በኩል እንደሚከፋፈል አስታውቀዋል።

የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል እንዲያግዝ ድርጅቱ ያደረገው ድጋፍ የመግዛት አቅም ለሌላቸው ማህበረሰብ ህይወት ለማዳን እንደሚረዳ   በመቀሌ ሐድነት ክፍለ ከተማ የህብርተሰብ ተጠቃሚነት ድጋፍ አስተባባሪ መምህር ገብረመድህን ካሳ ናቸው ።

ወቅቱ አቅም ያላቸው ወገኖች  ድጋፍ የሚሹበት መሆኑንም አመልክተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም