አገር አቀፉ የኮሮና ቫይረስ መከላከል ንቅናቄና ምርመራ ዘመቻ ተጀመረ

70

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 1/2012(ኢዜአ) አገር አቀፉ የኮሮና ቫይረስ መከላከል ንቅናቄና የምርመራ ዘመቻ በይፋ ተጀምሯል።
ንቅናቄው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በተገኙበት በይፋ ተጀምሯል።

የክልሎች ፕሬዚዳንቶችና ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት በንቅናቄና በምርመራ ዘመቻው መክፈቻ ላይ ተገኝተዋል።

'ማንም' በተሰኘው በዚህ አገር አቀፍ የኮሮና ቫይረስ መከላከል ንቅናቄና የምርመራ ዘመቻ በቀጣዮቹ ሁለት ሣምንታት 200 ሺህ ሰዎችን ለመመርመር፤ በቤት ለቤት ልየታም 17 ሚሊዮን ዜጎችን ተደራሽ ለማድረግ ታቅዷል።

የብሔራዊ የኮሮና ቫይረስ መከላከል የሚኒስትሮች ኮሚቴ የቫይረሱን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ ከቀናት በፊት ባካሄደው ውይይት ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ስለ ዘመቻው ገልጸው ነበር።

መንግስት ለዚህ ዘመቻ አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጉንም እንዲሁ።

በዘመቻው የሚገኘው ውጤት በቀጣዩ ዓመት ለሚከናወኑ ተግባራት አመላካች መነሻዎችን እንደሚሰጥና በተለይ ተማሪዎችና መምህራን በዘመቻው በመሳተፍ ጉልህ ሚና እንዲጫወቱም መልዕክት ተላልፏል።

የሃይማኖት አባቶችና የአገር ሽማግሌዎች እንዲሁም በየደረጃው ያሉ የማኅበረሰብ መሪዎች ለዘመቻው መሳካት የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡም ጥሪ ቀርቧል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም