እውነተኛ ፌዴራሊዝምና የመናገር ነፃነት ለውጦች ታይተዋል

108

አዲስ አበባ፣ሐምሌ 27/2012 (ኢዜአ) ባለፉት ሁለት አመታት ጊዜ ውስጥ እውነተኛ ፌዴራሊዝምና የመናገር ነፃነትን የሚያሳዩ ለውጦች በኢትዮጵያ ውስጥ መታየታቸው ተገለ። መንግስት በሁሉም የአገሪቱ አካባቢዎች እኩል የህግ የበላይነትና ፍትህ እንዲረጋገጥ ማስቻል እንዳለበትም ተገልጿል።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሰብዓዊ መብትና የፌዴራሊዝም  ዶክተር ሲሳይ መንግስቴ፣ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) ሊቀመንበር አቶ የሺዋስ አሰፋ እና በኦሮሚያ ክልል የብልፅግና ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ታዬ ደንደአ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ዙሪያ ከኢዜአ ጋር ቆይታ አድርገዋል።

በኢትዮጵያ የፖለቲካ ለውጥ ከመጣ በኋላ በተለያዩ ዘርፎች የመጡ ለውጦችን ማበረታታትና ጉድለቶች እንዲስተካከሉ የማድረግ ኃላፊነት የሁሉም ኢትዮጵያዊ መሆኑንም ተጠቅሷል።

ጉድለቶች ቢኖሩም ላለፉት ሁለት አመታት በኢትዮጵያ እውነተኛ የፌዴራሊዝም ስርዓት መታየቱን ዶክተር ሲሳይ መንግስቴ ተናግረዋል።

የፌዴራሊዝም ስርዓት በህግ ደረጃ ቢኖርም ክልሎች ራስን በራስ የማስተዳደር መብታቸውና በፌዴራል መንግስቱ ውስጥ ያላቸውን ውክልና አሟልቶ የተገበረ እንዳልነበረ አስታውሰዋል።

ክልሎች በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የመጣውን ለውጥ ተከትሎ ራስን በራስ ማስተዳደርና ሌሎች የፌዴራል ስርዓቱ የሚፈቅዱላቸው አሰራሮች እውን እየተደረጉ እንደሆነ ተናግረዋል።

ይህንን እውነታ በመካድ በአንዳንድ ምሁራን እውነታውን የካደ ሃሳብ እየተንጸባረቀ እንደሆነ አመልክተዋል።

በተለይም 'የመንግስት መዋቅር አሃዳዊ ነው፣ ፌደራሊዝም ስረዓት ፈርሷል' የሚለው ሃሳብ የተሳሳተ እንደሆነ አስገንዝበዋል።

የኢዜማ ሊቀመንበር አቶ የሺዋስ አሰፋ በበኩላቸው የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (ህወሃት) አመራሮች የተለያዩ ጉዳዮችን የሚያነሱት የሰሩትና እየሰሩ ያለው ወንጀል እንዳይነሳ አጀንዳ ለማስቀየር መሆኑን ገልጸዋል።

በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ማንኛውንም ሃሳብ ይዞ የሚመጣ የፖለቲካ ፓርቲ የሚሳተፍበት ምህዳር መመቻቸቱን አቶ የሺዋስ ጠቅሰዋል።

''ይሁን እንጂ የህወሃት አመራሮች ራሳቸው ባወጡትና ላለፉት አመታት ሲዳኙበት በነበረው ህግ ያለመዳኘት ሽሽት ይታይባቸዋል'' ብለዋል።

ከለውጡ ጎን ለጎን የኢትዮጵያውያንን ህይወት የሚፈታተኑና በህዝብ ተሳትፎና በመንግስት መስተካከል ያለባቸው ቀሪ ጉዳዮች መኖራቸውን ጠቁመዋል።

በተለይም የህዝቦችን ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሶ የመስራት፣ ሰላምንና የህግ የበላይነትን በሁሉም አካባቢዎች ማረጋገጥ ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገቡ ስራዎች መሆናቸውን ተናግረዋል።

''መንግስት ለውጡን ተከትሎ ከአገር ውጭ ያሉ የተለያየ አመለካከት ያላቸው ፓርቲዎች እንዲገቡ እስካደረገ ድረስ ይህን መምራት የሚችል ጠንካራ መዋቅር መፍጠር አለበት'' ብለዋል።

የኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ታዬ ደንደአ በበኩላቸው በአንዳንድ ተቃዋሚ ሃይሎች አመለካከት የመንግስትና የፓርቲ ስራን ያለማለያየት ችግር እንደሚታይ ተናግረዋል።

በተለይም ገዥው ፓርቲ በህዝብ ደህንነትና ሰላም፣ በኢኮኖሚና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ የሚሰራቸውን ስራዎች እንደ ፓርቲ ስራ አድርገው ሲያጥላሉ የሚታዩ አካላት መኖራቸውንም ጠቅሰዋል።

እነዚህ አመለካከቶች በሃይል እስካልተተገበሩ ድረስ የሃሳብ ሃሳብን ማራመድ ክፋት እንደሌለውም ተናግረዋል።

ከህግ ማስክበር ጎን ለጎን ህዝቡ የሚጠቅመውን መምረጥ ሲጀምር ሁሉም እየተስተካከለ እንደሚመጣ አመልክተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም