በሲዳማ ክልል145 ሺህ ሄክታር መሬት የማልማት ስራ እየተካሔደ ነው

58

ሐምሌ 27/2012 (ኢዜአ)በሲዳማ ክልል በዘንድሮው የመኽር አዝመራ 145 ሺህ ሄክታር መሬት የማልማት ስራ እየተካሔደ ነው ።

የክልሉ ግብርና ቢሮም   በምርት ዘመኑ 16 በመቶ የምርት እድገት ለማስመዝገብ ታቅዶ ወደ ስራ መገባቱን አስታውቋል።

በክልሉ ሸባዲኖ ወረዳ የሳዴቃ ቀበሌ አርሶ አደር ዳባላ ዳሣ በሰጡት አስተያየት እየጣለ ያለውን የክረምት ዝናብ በመጠቀም በአንድ ሄክታር ይዞታቸው ላይ  የተለያዩ አትክልቶችን ለማልማት የእርሻ ዝግጅት እያደረጉ  ነው።  

ሌላኛው የወረዳው አርሶ አደርነመተካ መሮ ከኮሮና እየተጠነቀቁ የቤተሰብ ጉልበት በመጠቀም በአንድ ነጥብ አምስት ሄክታር ማሳቻው ላይ ቦሎቄ፣ጤፍና ስንዴ ለማልማት መሬታቸውን ደጋግመው በማረስ እያለሰለሱ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የሲዳማ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ መስፊን ቃሬ ዋና ዋና ሰብሎችን ጨምሮ በአጠቃላይ በክልሉ ከ145 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር ለመሸፈን ታቅዷል።   

አቶ መስፊን ቃሬ በወረርሽኙ ሳቢያ የምርት መቀነስ እንዳያጋጥም 5 ሺህ ሄክታር  አዲስ መሬትን ልማት ውሰጥ በማስገባት በምርት ዘመኑ 16 በመቶ የምርት እድገት ለማስመዝገብ ርብርብ እየተደረገ ይገኛል ብለዋል። 

 እስካሁን ከ160 ሺህ ኩንታል በላይ ማዳበሪያና ምርጥ ዘር ለአርሶ አደሩ መሰራጨቱን የጠቀሱት አቶ መስፍን  ግብአቱ 85 በመቶ የሚሆነውን ፍላጎት የሸፈነ ቢሆንም  ቀሪውን  ለማቅረብ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየተነጋገሩ መሆናቸውን አመልክተዋል። 

በክልሉ ከአጠቃላይ የግብርና ልማት እንቅስቃሴው 3 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም