707 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው፤ የ28 ሰዎች ሕይወትም አልፏል

59

ሐምሌ 26/2012 (ኢዜአ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 7 ሺህ 607 የላብራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ 707 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸውና የ 28 ሰዎች ህይወት ማለፉን የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትረት ዶ/ር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።

በዚህም በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 18 ሺህ 706 ደርሷል።

እንዲሁም የተጨማሪ የ28 ሰዎች ህይወት በቫይረሱ ምክንያት ያለፈ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 310 መድረሱም ታውቋል።

በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት 406 ሰዎች ከቫይረሱ ያገገሙ ሲሆን በዚህም በአጠቃላይ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 7 ሺህ 6 01 ደርሷል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም