ኢዜአ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባበረከተው አስተዋጽኦ ዕውቅና ተሰጠው

57

አዲስ አበባ፣ ሀምሌ 26/2012 የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት(ኢዜአ) በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባበረከተው የማህበረሰብ ማንቃትና ቅስቀሳ ሥራ ዛሬ ዕውቅና አገኘ። 

ኢዜአ ዕውቅና የተሰጠው ዛሬ ''ድምጻችን ለግድባችን'' በሚል በተዘጋጀው  መርሐ ግብር በመገናኛ ብዙኃን (ሚዲያ) ዘርፍ ባበረከተው ሚና ነው።

ኢዜአ በግድቡ ዙሪያ ዜናዎች፤ ዘጋቢ ፕሮግራሞችንና የውይይት መድረኮችን ከማዘጋጀት በተጨማሪ ከግድቡ ግንባታ ሕዝባዊ ማስተባበሪያ ምክር ቤትና ከኢትዮጵያ ዳያስፖራዎች ማህበር ጋር በመተባበር ሲሰራ ቆይቷል።

የግድቡ የመጀመሪያ ዙር የውሃ ሙሌት ሐምሌ 15 ቀን 2012 መከናወኑ ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም