በሚሊዮን የሚቆጠሩ ላቲን አሜሪካውያን የርሃብ አደጋ ያሰጋቸዋል

121

ሐምሌ 23/2012  (ኢዜአ) በኮቪድ -19 ምክንያት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ላቲን አሜሪካውያን የርሃብ አደጋ እንደሚያሰጋቸው ተነግሯል፡፡

የተባባሩት መንግሥታት የምግብ ፕሮግራም (WFP) እንዳስጠነቀቀው፤ ኮቪድ-19 ያስከተለው የምጣኔ ሃብት ቀውስ በትንሹ 14 ሚሊዮን ላቲን አሜሪካውያን ላይ የርሃብ አደጋ ጋርጦባቸዋል፡፡

አገራት የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር የእንቅስቃሴ ገደቦችን እያጠናከሩ እና እያስፋፉ እንደሚገኝ የአልጄዚራ ዘገባ አመልክቷል፡፡

በላቲን አሜሪካ አገራት ከ4 ነጥብ 4 ሚሊዮን የሚልቁ ዜጎች በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሲሆን ከ185 ሺህ በላይ ሰዎች ደግሞ መሞታቸውን መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም