ባንኩ 1ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር አተረፈ

57

አዲስ አበባ ሀምሌ 20/2012(ኢዜአ) የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከታከስ በፊት 1 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር ማትረፉን ገለጸ።

በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ጉዳት ለገጠማቸው ወገኖች 310 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አድርጌያለሁ ብሏል።

የባንኩ ፕሬዘዳንት አቶ ደርቤ አስፋው ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ  ባንኩ ካለፈው በጀት ዓመት በ102 በመቶ የበለጠ ትርፍ አግኝቷል።

በበጀት ዓመቱ የተመዘገበው ትርፍ ለመጀመሪያ ጊዜ ከአንድ ቢሊዮን ብር መብለጡንም አመልክተዋል።

ባንኩ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ችግር በመቋቋም ባደረገው እንቅስቃሴ 9 ነጥብ 34 ቢሊዮን ብር  በማሰባሰብ አጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘብ 45 ነጥብ 52 ቢሊዮን ማድረሱን አስረድተዋል።

ባንኩ 3 ነጥብ 73 ቢሊዮን ብር ማበደሩን ፕሬዚዳንቱ አስታውቀዋል።

የሀብት መጠኑ በዓመቱ ውስጥ በ11ነጥብ 13 ቢሊዮን ብር አድጎ አጠቃላይ ሀብቱ 52 ነጥብ 92 ቢሊዮን ብር መድረሱን አቶ ደርቤ ተናግረዋል።

በበጀት ዓመቱ 31 ቅርጫፎችን መክፈቱን የገለጸው ባንክ፤ከመካከላቸው 13ቱ ከወለድ ነፃ አገልግሎት እንደሚሰጡ ገልጸዋል።

ባንኩ ማህበራዊ ሃላፊነቱን ለመወጣት በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ለተቸገሩ ወገኖች የ310 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉን አስታውቀዋል።

ወረርሽኙ በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ ላይ ያደረሰውን ጫና ለመቀነስ ብድር የወሰዱ ደንበኞች ለሦስት ወራት ከወለድ ነፃ ማድረጉን ፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል።  

የባንኩ 420 ቅርንጫፎችና 6ሚሊዮን ደንበኞች እንዳሉትም ታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም