የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት ጉባኤ በመጪው ቅዳሜ ይጀመራል

52

አሶሳ፤  ሐምሌ 15/2012 ( ኢዜአ) የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ምክር ቤት አምስተኛ የስራ ዘመን 11ኛ መደበኛ ጉባኤ በመጪው ቅዳሜ እንደሚጀመር የምክር ቤቱ ዋና አፈ ጉባኤ አስታወቁ።
ዋና አፈ ጉባኤው  አቶ ታደለ ተረፈ ዛሬ ለኢዜአ እንደገለጹት ጉባኤው ከመጪው ቅዳሜ ጀምሮ ለሁለት ቀናት በአሶሳ ከተማ ይካሄዳል።

በጉባኤው  የ2012 በጀት ዓመት  የጠቅላይ ፍርድ ቤት እና ዋና ኦዲት ቢሮ ጨምሮ  የክልሉ  ስራ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ወይይት ይደረግበታል ብለዋል።

የ2013  የስራ ዘመን  ዓመታዊ በጀት እንደሚጸድቅም ይጠበቃል።

በጉባኤው ማጠቃለያ  በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረው ሁለተኛው  የአረንጓዴ አሻራ  ልማት  አካል የሆነ ችግኝ የመትከል መረሃ ግብር እንደሚካሄድ   አቶ ታደለ ጨምረው ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም