ዚምባብዌ በኮሮና ቫይረስ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅን የተላለፉ 105 ሺህ ሰዎች በቁጥጥር ስር አዋለች

43

አዲስ አበባ 13/2012 (ኢዜአ) በዚምባብዌ በኮሮና ቫይረስ የወጣው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅን የተላለፉ 105 ሺህ ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ ፡፡

በዚምባብዌ ከመጋቢት ጀምሮ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ለመቆጣጠር የወጣውን ህግ የተላለፉ 105 ሺህ ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው የአገሪትዋ ፖሊስ ገለፀ፡፡

ምንም እንኳን አንዳንድ አክትቪስቶች እየተወሰደ ያለው እርምጃ ፖለቲካዊ ነው ቢሉም መንግስት ግን ዜጎች ከቫይረሱ ለመታደግ ያደረገው እንደሆነ ያነሳል፡፡

በአሁኑ ሰአት አጠቃላይ ከተለያዩ የአለም አገራት ወደ ዚምባብዌ ሲገቡ መንግስት እውቅና በሰጣቸውና አገልግሎቱ በሚሰጡ ቦታዎች ላይ ሶስት ሳምንት ኳረንቲን እንደሚቆዩ ያትታል፡፡

እንደፖሊስ መረጃ 276 ሰዎች በኳረንቲን ማእከል ላይ ሲሆኑ 30ዎቹ በቫይረሱ መያዛቸውና ለቤተሰቦቻቸውና ለማህበረሰቡ ጠንቅ በመሆናቸው ጉዳያቸው ወደ ፍርድቤት ተወስዷል፡፡

ሁለት ወንዶች ለሰባት የቤተሰቦቻቸው አባል በቫይረሱ እንዲያዙ ማድረጋቸውም የአገሪቱ ቴሌቪዥን ዘግቧል፡፡

ባለፉት ሁለት ቀናት በቁጥጥር ስር የዋሉት ሰዎች የፊት መሸፈኛ ማስክ ሳይጠቀሙ አላስፈላጊ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ የተገኙ ናቸው ተብሏል፡፡

በድብቅ ከፍተኛ የሰው ቁጥር ተጠቃሚ የሚያስተናግዱ የመጠጥ ቤቶች ባለቤቶች በቁጥጥር ስር እንዲውሉ እየተደረገ መሆኑንምየፖሊስ ቃል አቀባይ ፓውል ንያቲ ለቴሌቪዝኑ ጨምረው ተናግረዋል፡፡

እስካሁን ባለው መረጃ በአገሪቷ ከ 1,500 የሚበልጡ በቫይረሱ ተይዘው እንደሚገኙ በመረጃው ተጠቅሷል፡፡ ምንጭ፡-ቢቢሲ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም