በኢትዮጵያ ተጨማሪ 119 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው

42

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21/2012 ( ኢዜአ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገው 3 ሺህ 895 የላቦራቶሪ ምርመራ 119 ሰዎች የኮሮናቫይረስ የተገኘባቸው ሲሆን የ4 ሰዎች ህይወት አልፏል።

በአጠቃላይ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 5 ሺህ 689 ደርሷል።

ቫይረሱ የተገኘባቸው 73 ወንዶችና 46 ሴቶች ሲሆኑ፣ ከአንድ ዓመት ሕፃን እስከ 80 ዓመት አዛውንት ይገኙበታል።

በዜግነት 116 ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ 3ቱ የውጭ አገር ዜጎች ናቸው።

ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው 99 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ 7 ሰዎች ከሐረሪ፣ 5 ሰዎች ከትግራይ፣ 4 ሰዎች ከሶማሌ፣ 3 ከኦሮሚያና 1 ሰው ከአማራ ክልል ናቸው።

በእለቱ የ4 ሰዎች  ህይወት ያለፈ ሲሆን 1 በአስከሬን ላይ በተደረገ ምርመራ የተገኘ፣ 3ቱ ደግሞ በጤና ተቋም በሕክምና ላይ የነበሩ ናቸው።

በቫይረሱ ተይዘው ሕይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 98 ሲሆን፣ በጽኑ ሕመም ላይ የሚገኙት ደግሞ 33 ሰዎች  መሆናቸውን መረጃው ያመለክታል።

በሌላ በኩል በትናንትናው  እለት 117 ሰዎች (78 ከአዲስ አበባ፣ 35  ከትግራይ ክልል እና 4 ከድሬዳዋ ያገገሙ ሲሆን፣ በአጠቃላይ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 2 ሺህ 132 ደርሷል።

በኢትዮጵያ እስካሁን 246 ሺህ 911 የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጓል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም