ከ6 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች ተወገዱ

79

ሁመራ፣ ሰኔ 21/2012 (ኢዜአ) በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሁመራ ፍተሻ ጣቢያ ከተያዙ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መካከል 6 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር ግምት ያላቸው ቁሳቁሶች እንዲወገዱ መደረጉን ገለፀ ።

የጽህፈት ቤቱ አስተባባሪ ኮማንደር መሰለ ይማም እንደገለጹት በዘንድሮው የበጀት ዓመት ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በህገ ወጥ መንገድ ከአገር ሊወጡና ሊገቡ ሲሉ ተይዘዋል ።

ከተያዙት የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መካከል 6 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር ግምት ያላቸው የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈ መድሃኒቶች ፣ የታሸጉ ምግቦችና ካናቢስ የተባለ አደንዛዥ ዕፅ እንዲወገዱ ተደርገዋል ።

የሁመራ የምግብና መድሀኒት ቁጥጥር ኳራንታይን አስተባባሪ አቶ አስፋው ጥላሁን እንደገለፁት ከተያዙት የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መካከል እንዲወገዱ የተደረጉት በሃገር ኢኮኖሚ፣በሰላምና በሰዎች ጤንነት ላይ አደጋ የሚያስከትሉ መሆናቸው በመረጋገጡ ነው ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም