የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ወረርሽኙን ለመከላከል የድርሻውን እየተወጣ መሆኑን ገለጹ

52

ጋምቤላ፣ ሰኔ 20/2012(አዜአ) የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት በመደገፍ የድርሻውን እየተወጣ መሆኑን የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ገለጸ።

ዩኒቨርስቲው በጋምቤላ ከተማ አምስት ቀበሌዎች ለሚገኙ 150 አቅመ ደካሞች የምግብ ማጋራት መረሃ ግብር ጀምሯል።

በመረሃ ግብሩ ስነስርዓት የዩኒቨርሲቲው የማህበረሰብ፣ የምርምርና የኢንዱስትሪ ትስሰር ምክትል ፕሬዘዳንት ዶክተር ጋልዋክ ጋርኮት እንደተናገሩት የኮሮና ወረርሽኝ እያስከተለ ያለውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግር  ለመከላከል ተቋሙ ከክልሉ መንግስት ጋር እየሰራ ነው።

በዩኒቨርሲቲው የለይቶ ማቆያና የህክምና አገልገሎት መስጫ ማዕከል ከማቋቋም ጀምሮ ህብረተሰቡን ከወረርሽኙ ለመታገድ በቅንጀት ሲሰራ መቆየቱን አውስተዋል።

ተቋሙ የንዕህና መጠቢያ ሳኒታይዘር በማምረት ለህብረተሰቡ የማሰራጭት፣ ግንዛቤን የማሳደግ፣ ለአቅመ ደካሞች የሚሆን የምግብ ፍጆታዎችን የመደገፉን ስራዎች አከናውኗል ብለዋል።

በቀጣይም ዩኒቨርሲቲው የኮሮና ቫይረስ የምርመራ ናሙናዎች ለማሳደግ የሚስችል የላብራቶሪ ማዕከል ማቋቋም  እየሰራ መሆኑን ዶክተር ጋልዋክ አስታውቀል።

የዩኒቨርሲቲው የአስተዳደርና የተማሪዎች አገልግሎት ምክትል ፕሬዘዳንት ዶክተር አሸናፊ አሰፋ በበኩላቸው በክርምቱ ወራት በኮሮና ወረርሽኝ መከላከል፣ ማዕድ ማጋራ፣ የአረንጓዴ አሻራ ልማትና ደም ልገሳ ላይ በበጎ ፈቃደኝነት ለመሰማራት እንቅስቃሴ መጀመሩን  ተናግረዋል።

እንቅስቃሴውን የጀመሩትም በጋምቤላ ከተማ አምስት ቀበሌዎች ለሚገኙ 150 አቅመ ደካሞች ምግብ በማጋራት እንደሆነ ጠቅሰዋል።

ዩኒቨርሲተው በለይቶ ማቆያና የክህምና ማዕከል ለሚገኙ ወገኖችም ምግብ እያቀረበ  መሆኑን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም