የአፍሪካ ህብረት ዓባላት ቢሮ ፣ ኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብጽ ለሕዳሴ ግድብ ከአፍሪካ የመነጨ መፍትሔን ማበጀት ላይ ያተኮረ ውይይት አካሄደ

91

ሰኔ 19/2012(ኢዜአ) የአፍሪካ ህብረት ዓባላት ቢሮ፣ ኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብጽ ለታላቁ የሕዳሴ ግድብ ከአፍሪካ የመነጨ መፍትሔን ማበጀት ላይ ያተኮረ ውይይት ማካሄዳቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አስታወቁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ፅሁፍ ውይይቱ ውጤታማ እንደነበር ገልፀዋል፡፡

እንዲሁም ይህን አህጉራዊ ጠቀሜታ ያለው የከፍተኛ አመራሮች ስብሰባ ላስተባበሩት የአፍሪካ ህብረት ሰብሳቢ ፕሬዚደንት ሲሪል ራማፎሳ እና ለህብረቱ ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በፅሁፋቸው የፓን አፍሪካዊነት መንፈስ ያለው አህጉራዊ ተቋማችን ለአፍሪካ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያላቸውን ውይይቶች ለማካሄድ ትክክለኛው ሥፍራ ነው ሲሉም ገልፀዋል።

በተጨማሪም ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ሁሉም ባለ ድርሻ አካላት የላቀ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት እና የጋራ ብልጽግና የሚያገኙበትን ዕድል ይዟል ሲሉም ጽፈዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም