የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የህዳሴውን ግድብ ዋንጫን ከንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ይረከባል

66

አዲስ አበባ ሰኔ 16/2012 (ኢዜአ) የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ከ20 ቀናት በፊት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተረከበውን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ዋንጫን ዛሬ ለአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ዛሬ ያስረክባል፡፡

ዋንጫው በክፍለ ከተማው በቆየባቸው ቀናት 29 ሚሊዮን ብር ተሰብስቧል፡፡

ዋንጫው ወደ ክፍለ ከተማው ከማምራቱ በፊትም በክፍለ ከተማው ሦስት ሚሊዮን ብር ለግድቡ የተሰበሰበ ሲሆን፤ በአጠቃላይም 32 ሚሊዮን ብር ገቢ ሆኗል፡፡

በዛሬው ዕለትም ዋንጫውን ለአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ያሥረክባል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ዋንጫው በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በሚቆይበት ጊዜ  ለግድቡ ግንባታ ገቢ እንደሚሰባሰብ  ተገልጿል፡፡

የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ከከተማው አስተዳደሩ ዋንጫ የተረከበ የመጀመሪያው ክፍለ ከተማ ነው ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 10 ክፍለ ከተሞች አሉት።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም