በጀነራል ሰዓረ መኮንን ስም ጎዳና ተሰየመ

67

ሰኔ 15/2012 (ኢዜአ) ከቦሌ ሩዋንዳ ድልድይ እስከ አትላስ ያለው ጎዳና በጀነራል ሰዓረ መኮንን ስም ተሰየመ፡፡

የጀነራል ሰዓረ መኮንን 1ኛ ዓመት ዝክረ ሰማዕታት መታሰቢያ የችግኝ ተከላ መርሃግብር ተካሂዷል፡፡

የጀነራል ሰዓረ መኮንን 1ኛ ዓመት ዝክረ ሰማዕታት መታሰቢያ የችግኝ ተከላ መርሃግብር የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ እና ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ተከናውኗል፡፡

ጀነራል ሰዓረ ባለፈው አመት ህይወታቸው ከማለፉ ከሰዓታት በፊት ከኢ/ር ታከለ ኡማ ጋር በመሆን ከሩዋንዳ ወደ አትላስ በሚወስደው መንገድ ላይ ችግኝ በጋራ ተክለዋል።

የከተማ አስተዳደሩ ጀነራል ሰዓረ ህይወታቸው ሲያልፍ ቦታው ላይ ፓርክ ለማሰራት ይፋ ባደረገው መሰረት የመታሰቢያ ፓርክ ግንባታው በይፋ ተጀምሯል።

በተጨማሪም ከቦሌ ሩዋንዳ ድልድይ እስከ አትላስ ያለው ጎዳና በጀነራል ሰዓረ መኮንን ስም እንዲሰየም ተደርጓል፡፡

በስነስርዓቱ ላይ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች፤የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ፤የአዲስ አበባ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ተስፋዬ በልጅጌ፤የአዲስ አበባ አስተዳደር ምክር ቤት አፈጉባኤ ወ/ሮ አበበች ነጋሽ እንዲሁም የጀነራሉ ቤተሰቦችና የስራ ባልደረቦቻቸው ተገኝተዋል ። መረጃው የአ/አ ከንቲባ ፕሬስ ሴክሬተሪ ነው

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም