ሱዳን በህዳሴ ግድብ ላይ ያለኝ አቋም ፍትሃዊ የውሃ አጠቃቀም ላይ የተመሠረተ ነው አለች

58

ሰኔ 11/2012(ኢዜአ) ሱዳን በህዳሴ ግድብ ላይ ያላትን አቋም ፍትሃዊ የውሃ አጠቃቀም ላይ የተመሠረተ እንደሆነ የሱዳን የመስኖና የውሃ ሀብት ሚኒስትር ገለፁ፡፡

ሱዳን የህዳሴ ግድብ ግንባታ ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ በመሰረታዊ አለም አቀፍ ህግጋት መሰረት ሌሎች አገራት በማይጎዳ መልኩ በፍትሃዊና ምክንያታዊ የውሃ ክፍፍል እንደምትደግፍ የመስኖና የውሃ ሀብት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ያሰር አባስ ገልፀዋል፡፡

የሰባተኛ ቀን የድርድር ውጤቱን በማስመልከት ለሱዳን ዜና አገልግሎት እንደገለፁት ሱዳን በሶስትዮሽ ውይይቱ እየተፈጠሩ ያሉ ልዩነቶችን በውይይት መፍትሄ እንዲያገኙ በመስራት የቀድሞ አቋሟ በመያዝ ድጋፏን እንደምትቀጥል ነው ፐሮፌሰሩ የተናገሩት፡፡

ኢትዮጵያ አለም አቀፍ ፍትሃዊ የውሃ አጠቃቀም ህጉን በማክበር ከህዳሴ ግድብ የሚመነጨውን የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ሃይል መጠቀም ሙሉ መብት እንዳላት ሱዳን እምነትዋን ገልፃለች፡፡

ባለለፉት አመታት በነበረው ተሳትፎዋም በመካከል ሊፈጠሩ የሚችሉት አለመግባባቶች የመፍትሄ አካል ለመሆን ጥረት ማድረግዋ ነው ፕሮፌሰሩ የጠቀሱት፡፡

ሚኒስትሩ አክለውም ባለፉት ጊዜያት የነበሩም ሆነ የዛሬው የሶስትዮሽ ድርድርና ውይይቶቹ በአንዳንድ ነጥቦች ላይ አለመግባባቶች ቢኖርም በአብዛኛው አዎንታዊ እና ወንድማማችነት የተሞላበት ውይይት መደረጉ ተናግረዋል።

ፕሮፌሰር ያሰር እንደሚሉት ከመጀመርያ ሙሌት ቴክኒካል ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ከ90-95 ስምምነት ላይ የተደረሰ ሲሆን ከህዳሴ ግድቡ ሙሌት በኋላ ያሉ ቴክኒካል ጉዳዮች አለመግባባት የተፈጠረ ቢሆንም ውስብስብ እና አስቸጋሪ ጉዳዮች አይደሉም፡፡

ስምምነቱ ከተፈረመ በኋላ በተለይም በስምምነቱ ሕጋዊ አካል በኩል በየጊዜው የእይታ ለውጦች ማስተዋላቸው ነው የጠቆሙት፡፡

የህዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌትና አሠራር በሶስቱ ሀገራት መካከል የውሃ መጋራትን በተመለከተ ስምምነት ላይ መድረስ የሚያስችል አመለካከት ማሳደግ እንደሚያሰፈልግም ነው ያብራሩት፡፡

በመጀመርያ የውሃ ሙሌትና አመታዊ የውሃ አለቃቀቅ ላይ ትኩረቱን አድርጎ በኢትዮጵያ፣ በሱዳንና ግብፅ መካከል በቪዲዮ ኮንፈረንስ ትናንት መኬሄዱ ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም