የቻይና አፍሪካ ልዩ ጉባኤ ሊካሄድ ነው

66

ሰኔ 9/2012(ኢዜአ) የቻይና አፍሪካ ጥምረት ኮቪድ 19ን ለመከላከል  በሚል የሚደረገውን ልዩ ጉባኤ የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂን ፒንግ ይመሩታል ሲል የዘገበው ሺንሁዋ ነው።

ጉባኤው በቻይና አዘጋጀነት በርእሰ ከተማዋ ቤጂንግ የሚደረግ ሲሆን ሙሉ ትኩረቱም የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላከል አፍሪካና ቻይና ስለሚኖራቸው ትብብር እንደሚሆን የቻይና ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ቃል አቀባይ ሁዋ ቹንዪንግ አስታውቀዋል።

የልዩ ጉባኤው አስፈላጊነት ሃሳብ የመጣው ከቻይና መሆኑን ያነሳው ዘገባው የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር የሆኑት ደቡብ አፍሪካና ምክትሏ ሴኔጋል ስለተስማሙበት ነው ተብሏል።

በቪዲዮ ኮንፈሰንስ በሚካሄደው በዚሁ ጉባኤ የአፍሪካ ህብረት ከፍተኛ ሃላፊዎች፣ የሀገራት መሪዎችና የክፍለ አህጉራት ድርጅቶች አመራሮች እንደሚሳተፉ ይጠበቃል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ  አንቶኒዮ ጉቴሬዝና የአለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተርም በልዩ ተጋባዥነት በጉባኤው እንደሚታደሙም ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም