ዩኒቨርሲቲው ችግር ፈቺ የፈጠራ ስራዎችን ለተጠቃሚዎች ለማድረስ እየሰራ መሆኑን ገለፀ

65
ባህር ዳር ሰኔ 30/2010 በምርምር የሚወጡ ችግር ፈቺ የፈጠራ ቴክኖሎጂዎችን ለተጠቃሚዎች ተደራሽ ለማድረግ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ። በዩኒቨርሲቲው የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ኢንዱስትሪ ትስስርና ማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክተር ዶክተር ሲሳይ ገረመው ለኢዜአ እንደገለጹት ኢንስቲትዩቱ ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ በመምህራንና በተመራቂ ተማሪዎች 200 የሚደረሱ የፈጠራ ስራዎች ወጥተዋል። ከወጡ የፈጠራ ስራዎች ውስጥም 50 የሚደርሱት በዚህ ዓመት ተመራቂ በሆኑ የመካኒካል፣ ኤሌክትሪካልና በሌሎች የኢንጅነሪንግ ተማሪዎች ለመመረቂያ ሟሟያ የወጡ የፈጠራ ቴክኖሎጅዎች መሆናቸውን ገልጸዋል። እስካሁን ከወጡትም 20 የሚሆኑት የበቆሎ መዝሪያና መፈልፈያ፣ የጠብታ መስኖ፣ የተሻሻሉ ማረሻዎችና ሌሎች ችግር ፈቺ የፈጠራ ስራዎች ለተጠቃሚች እንዲደርሱ ተደርጓል። ጥቅም ላይ ያልዋሉ ቀሪ የፈጠራ ስርዎችንም በቀጣይ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመገናኘት ጥቅም ላይ እንዲውሉ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑንም አስረድተዋል።  በዩኒቨርሲቲው የመካኒካል ኢንጅነሪንግ የመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂ ተማሪ አለልኝ ደመቀ በሰጠው አስተያየት መኖ ማቀነባበርና በቆሎ የመፈልፈል ስራን በአንድ ላይ የሚያከናውን የፈጠራ ስራ ሦስት ተማሪዎች በመመረቂያነት ሰርተው ማቅረባቸውን ገልጿል፡፡ በባህላዊ መንገድ ለእንስሳት ከሚቀርበው መኖ 25 በመቶ የሚሆነው እንደሚባክን ገልፆ ሰርተው ያቀረቡት የእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያና የበቆሎ መፈልፈያ ቴክኖሎጂ ብክነትን መቶ በመቶ እንደሚያስቀር አስታውቋል፡፡ ቴክኖሎጅውም ንጥረ ነገሮችን በውስጡ የያዘ አምስት ኩንታል የእንስሳት መኖን በሰዓት አድቅቆ ማዘጋጀት የሚችል ከመሆኑም በላይ በተመሳሳይ ሰዓትም 10 ኩንታል በቆሎ መፈልፈል እንደሚችል ገልጿል። ቴክኖሎጂው ከጠፍጣፋ ብረት የተሰራና በቤንዚን የሚሰራ በመሆኑ በቀጣይ ከተለያዩ ተቋማት ጋር ተቀራርበን ቴክኖሎጂውን በማባዛት ለተጠቃሚ አርሶ አደሮች በተመጣጣኝ ዋጋ እንደሚያቀርቡ አስታውቋል፡፡ የአርሶ አደሩን ጊዜ፣ ጉልበትና የምርት ብክነትን መቀነስ የሚያስችል የጤፍ መውቂያና ማበጠሪያ ቴክኖሎጂ እንዳፈለቁ የተናገረው ደግሞ ሌላኛው የመካኒካል ኢንጂነሪንግ ተመራቂ ተማሪ አበበ ተፈራ ነው። ሦስት ሆነው ለመጀመሪያ ዲግሪ መመረቂያ ማሟያ ሰርተው ያቀረቡት የፈጠራ ስራ የጤፍ ምርትን ከገለባው በመለየትና በማበጠር በሰዓት ስድስት ኩንታል ምርት ማዘጋጀት እንደሚያስችል ገልጿል። ቴክኖሎጂው አዋጭና ተፈላጊ በመሆኑም ከሚመለከተው አካል ጋር ተቀናጅተው በማባዛት ለአርሶ አደሩ በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ የሚታየውን የምርት ጥራትና ብክነት ችግር ለመቅረፍ እንደሚሰሩም ተማሪ አበበ አስረድቷ  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም