ባለስልጣኑ 15 የመንገድ ፕሮጀክቶችን ለመስራት የውል ስምምነት ተፈራረመ

85

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 4/2012( ኢዜአ) የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ከ25 ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ 15 የመንገድ ፕሮጀክቶችን ለመስራት የሚያስችል የውል ስምምነት ተፈራረመ።

የመንገድ ፕሮጀክቶቹ በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የሚገነቡ ሲሆን በጠቅላላው 1ሺህ 22 ኪሎ ሜትር ርዝመት እንዳላቸው ተገልጿል።

የመንገድ ፕሮጀክቶቹ ወጪ 25 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ሲሆን ሙሉ ለሙሉ በኢትዮጵያ መንግስት እንደሚሸፈንም በውል ስምምነት መርሃግብሩ ላይ ተመልክቷል።

ከሚገነቡት መንገዶች 13ቱ በአስፋልት ኮንክሪት የሚሰሩ ሲሆን አንድ የጠጠር መንገድ ግንባታና አንድ ከባድ የመንገድ ጥገና ሥራን በፕሮጀክቱ ተካተዋል።

በመንገዶቹ ግንባታ ሥራ ሰባት የአገር ውስጥና ሌሎች የውጭ አገር ሥራ ተቋራጮች እንደሚሳተፉ ታውቋል።

የግንባታ ሥራዎችም ከአንድ ዓመት ከስድስት ወር እስከ አራት ዓመት ባለው ጊዜ እንደሚጠናቀቁ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም