የአገሪቱ የ 2013 ረቂቅ በጀት ላይ ውይይት እየተደረገ ነው

68

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4/2012(ኢዜአ) ለኢትዮጵያ የ2013 በጀት ዓመት በቀረበው 476 ቢሊዮን ብር ረቂቅ በጀት ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው። ኢኮኖሚው በቀጣየ በጀት ዓመት 8 ነጥብ 5 በመቶ ዕድገት እንደሚያስመዘግብ የገንዘብ ሚነስትሩ ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አምስተኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አምስተኛ ዓመት የሥራ ዘመን 16ኛ መደበኛ ስብሰባ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አዳራሽ እየተካሄደ ነው።

ምክር በቱ በማካሄድ ላይ ባለው መደበኛው ስብሰባው  የአራተኛናና  አምስተኛ ልዩ  ስብሰባዎች ቃለ ጉባዔዎችን መርምሮ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡

ምክር ቤቱ የኢፌዲሪ የገንዘብ ሚኒስትር  አቶ አህመድ ሺዴ የፌዴራል መንግሥት የ2013 ረቂቅ በጀት በተመለከተ በሚያቀርቡት የበጀት መግለጫ በማድመጥ ላይ ይገኛል፡፡

በአገሪቱ  ከ2008 በጀት ዓመት ጀምሮ ተቀዛቅዞ የነበረው ኢኮኖሚ እያንሰራራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

መንግሥት የማክሮ ኢኮኖሚው ከገጠመው ተግዳሮት ለማላቀቅ አገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ቀርጾ በመተግበር ላይ እንደሚገኝ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

በጀቱ ግብዓትን ከውጤት ጋር የሚያዛምድ እንዲሁም የኮሮና ቫይረስ የሚያስከትለውን ተጽዕኖ መቋቋምን ታሳቢ ተደርጎ መዘጋጀቱን  አመልክተዋል፡፡

በቀጣዩ በጀት ዓመት ኢኮኖሚው  በ8 ነጥብ 5 በመቶ ዕድገት ያስመዘግባል ተብሎ እንደሚጠበቅ  አቶ አህመድ አስታውቀዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም