የካሌድ ዲጆ መስኖ ልማት ፕሮጀክት የግንባታ ስምምነት ተፈረመ

98

ሰኔ 02/2012 (ኢዜአ) በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል፣ ስልጤ ዞን በ1 ነጥብ 19 ቢሊዮን ብር የሚገነባው የካሌድ ዲጆ መስኖ ልማት ፕሮጀክት የግንባታ ስምምነት በውኃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ተፈርሟል።

የመስኖ ልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ሚካኤል መሐሪ እና የደቡብ ውኃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ዋና ሥራአስፈጻሚ አቶ ኤልያስ ቱሮ ስምምነቱን ፈርመዋል።

በፊርማ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የውኃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ ተቋራጭ ፕሮጀክቱ በተያዘለት ጊዜ በጥራት ተገንብቶ እንዲጠናቀቅ የክልሉ መንግሥት እና የዞኑ አስተዳደር ድጋፍ እንዲሁም የተቋራጩ ጥረት አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል።

የፕሮጀክቱ ግንባታ ሲጠናቀቅ 1ሺህ 800 ሔክታር መሬት ማልማት እንደሚችል ከውኃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ጠቁሟል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም