የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ 9 ሺህ 724 ተማሪዎችን አስመርቋል

69
አዲስ አበባ ሰኔ 30/2010 አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛ፣ በማታ፣ በርቀትና በክረምት መርሃ ግብር ያስተማራቸውን 9 ሺህ 724 ተማሪዎች ዛሬ አስመርቋል። በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ በመካሄድ ላይ ባለው የምርቃት  ስነ-ስርዓት ላይ በመመረቅ ላይ ካሉ ተማሪዎች  መካከል -ወንዶች 6ሺ956 -ሴቶች 2ሺ 768  ሲሆኑ ከዚህ ውስጥ -በመጀመሪያ ዲግሪ 6ሺ044 -በሁለተኛና በሶስተኛ ዲግሪ 3ሺ680 ሲሆኑ ከዚህ ውስጥ 251 የዶክትሬት ዲግሪ ተመራቂዎች ናቸው፡፡ -አካል ጉዳተኞች  ዜጎች  450  እንደሆኑና -200 የሚሆኑት ደሞ የውጭ ሀገር ዜጎች  ናቸው ተብሏል በዛሬው እለት የወርቅ ሜዳሊያ ይሸለማሉ ተብለው ከሚጠበቁት 12 ተመራቂዎች መካከል ሰባቱ ሴቶች  ናቸው። ዩኒቨርሲቲው በዚህ ዓመት የክብር ዶክትሬት ዲግሪ እንደማይሰጥም ተገልጿል። ዩኒቨርሲቲው ከምስረታው ጀምሮ 236 ሺህ 378 ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡ በዚህ ዓመት አጠቃላይ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች  170 ሺህ 578 ተማሪዎችን የሚያስመርቁ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ደግሞ 32 በመቶዎቹ ሴቶች ናቸው፡፡
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም