ሚኒስቴሩ ከ25 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ ለኮሮና መከላከያ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

68

አዲስ አበባ ግንቦት 26/2012 (አዜአ) የከተማና ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ከ25 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው ለኮሮና መከላከያ የሚውሉ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።

ድጋፉን ለክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች አከፋፍሏል።

ድጋፉ በዋናነት በደረቅ ቆሻሻ ማስወገድ ሥራ ለተሰማሩና ለኮንስትራክሽን ሠራተኞች ይውላል።

ከዓለም ባንክ ጋር በመተባበር የተሰጠው ድጋፍ ጭምብል፣ የንጽህና መጠበቂያዎችንና የሙቀት መለኪያ መሣሪያዎችን ያካትታል።

የከተማና ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር ኢንጅነር አይሻ መሐመድ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት ድጋፉ በኮንስትራክሽን ሥራዎች የተሰማሩ ሰራተኞች ራሳቸውን ከበሽታው ጠብቀው እንዲሰሩ መሰጠቱን አስታውቀዋል።

ፕሮጀክቶችን ኃላፊነት በተሞላበት መልኩ ማከናወን እንደሚገባም አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ መንግሥትና ከዓለም ባንክ ጋር በመተባበር የሥራ ዕድል ፈጠራና ስልጠናን ያካተቱ ፕሮግራሞች ያካሂዳሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም