ድርጅቱ ሶስት ሚሊዮን 800ሺህ ብር ግምት ያላቸው ቁሰቁሶች ድጋፍ አደረገ - ኢዜአ አማርኛ
ድርጅቱ ሶስት ሚሊዮን 800ሺህ ብር ግምት ያላቸው ቁሰቁሶች ድጋፍ አደረገ
57
ግንቦት 26/2012 (ኢዜአ) በተባበሩት መንግስታት የህጻናት መርጃ ድርጅት/ዩኒሴፍ/ ኮሮናን ለመከላከል የሚያግዙ ሶስት ሚሊዮን 800ሺህ ብር ግምት ያላቸው ቁሳቁሶች ለትግራይ ክልል ሁለት ተቋማት ድጋፍ አደረገ።
ድርጅቱ ድጋፉን ያደረገው ለክልሉ ጤና እና ውሃ ሃብት ቢሮዎች ነው።
ለሁለቱ ተቋማት ከተደረገው ድጋፍ ውስጥ ትላልቅ የውሃ ማጠራቀሚያ ጋኖች/ሮቶ/ እና የተለያዩ የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች ይገኙበታል።
ድጋፉ ለከተሞች እና ገጠር ወረዳዎች በማህበራዊ ረዲኤት ትግራይ /ማረት/ አማካይነት እንደሚከፋፈል ትናንት ርክክብ በተካሄደበት ወቅት የክልሉ ውሃ ሃብት ቢሮ ኃላፊ ኢንጅነር ቴድሮስ ገብረእግዚአብሔር ገልጸዋል።
ዩኒሴፍ ባለፈው ዓመት ለንፁህ መጠጥ ውሃና ሌሎች የልማት ስራዎች ድጋፍ የሚውል 16 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉንም አውስተዋል።
የክልሉን ጤና ቢሮ ተወካይ አቶ ሙሉጌታ ቸርነት በበኩላቸው የድርጅቱ ድጋፍ በክልሉ የኮሮና ቫይረስ ስጋት ላለባቸው አካባቢዎች እንደሚሰጥ ተናግረዋል።
''ድጋፋችን የመጀመሪያ እንጂ የመጨረሻ አይደለም፤ በቀጣይም እንሰራለን " ያሉት ደግሞ በዩኒሴፍ የትግራይ ክልል ተወካይ ሚስተር ጋሳን ማዲህ ናቸው።