አቶ ርስቱ ይርዳው በሃላባ ዞን የልማት እንቅስቃሴዎችን እየጎበኙ ነው

89

ሀዋሳ፣ ግንቦት 26/2012 (ኢዜአ) የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ርስቱ ይርዳው በሃላባ ዞን የበልግ አዝርዕት ልማት እንቅስቀሴዎችን በመስክ እየጎበኙ ነው።

በአሁኑ ወቅት በዞኑ አቶቲ ወረዳ ያዮ ቀበሌ ገበሬ ማህበር በመገኘት በኩታ ገጠም የለማውን የበቆሎ ሰብል እየተመለከቱ ይገኛሉ።

በቀጣይም በወረዳው ለአርንጓዴ አሸራ ልማት የሚተከል የችግኝ ዝግጅት ተዘዋውረው እንደሚጎበኙ የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ዳንኤል ዳምጠው ገልጸዋል።

በተጨማሪም ሃላባ ዞን የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል እየተካሄደ ያለውን የስራ እንቅስቃሴም እንዲሁ።

ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በሌሎችንም የክልሉ  ዞኖች ተመሳሳይ የመስክ ጉብኝት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም