በ361 ሚሊዮን ብር የተገነቡ መንገዶች ለአገልግሎት በቁ

98

 አዲስ አበባ  ግንቦት 23/2012 (ኢዜአ) በአዲስ አበባ 361 ሚሊዮን ብር ወጪ የተደረገባቸው አራት መንገዶች ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ሆኑ።

የመዲናዋ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ዑማ እና የአስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች መንገዶቹን አስመርቀዋል።

ለአገልግሎት ክፍት የሆኑት መንገዶች ከኢትዮ-ፓረንት ስኩል እስከ ዩኒቲ ዮኒቨርሲቲ ጋራዥ፣ ከጅቡቲ ኤምባሲ ሰሚት ኮንዶሚኒየም፣ ከአራብሳ ኮንዶሚኒየም አያት ኮንዶሚኒየም እና ከሲኤምሲ-ሰሚት-አያት የሚወስዱ ናቸው።

የመንገዶቹ አጠቃላይ ርዝመት 6 ነጥብ 8 ኪሎ ሜትር ሲሆን 15 ሜትር የጎን ስፋትም አላቸው።

የመንገዶቹ መጠናቀቅ ለአካባቢዎቹና ለከተማዋ ነዋሪዎች ማኅበራዊ እንቅስቃሴ ምቹነት ጉልህ ፋይዳ እንዳለው ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም