የተጀመረው የመደመር ጉዞ ቀጣይነት እንዲኖረው የኅብረተሰቡ ድጋፍ እንዲቀጥል ተጠየቀ

65
አዲስ አበባ ሰኔ 29/2010 የተጀመረው የይቅር ባይነት፣ የፍቅር፣ የአንድነትና የመደመር ጉዞ ቀጣይነት እንዲኖረው ኅብረተሰቡ እስካሁን ያደርግ የነበረውን ድጋፍና ትብብር አጠናክሮ  እንዲቀጥል  መንግሥት ጥሪ አቀረበ። የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ለኢዜአ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ መንግሥት ነባራዊ የኢትዮጵያን ሁኔታ ታሳቢ በማድረግ የዴሞክራሲ ምህዳሩን ለማስፋት እየሰራ ነው። ሕጉን ለሁሉም ኃይሎች እኩል ለማድረግ ቀን ከሌት በመታተር ላይ እንደሆነ ያመለከተው መገለጫው ''ይህ የመንግሥት ቀና አካሄድ ለአንዳንድ ኃይሎችና ግለሰቦች ምቾት አልሰጠም'' ብሏል። በእንዲህ ያለ ኋላ ቀር የፖለቲካ አካሄድና አስተሳሰብ የተዘፈቁ ኃይሎች ህዝብን ከህዝብ ለማጋጨት ከሚያደርጓቸው ሴራዎች ባሻገር ህዝቦች በለውጥ ሂደቱ ላይ ጥርጣሬ እንዲያድርባቸው እየሰሩ መሆናቸውን ጠቁሟል። መንግሥት እየተፈፀሙ ያሉ የፖለቲካ ደባዎችን በሆደ ሰፊነት ማለፍን የመረጠው አገራዊ  መግባባትንና አንድነትን ለማጎልበት ካለው ጽኑ አቋም እንጂ እየተፈፀሙ የፖለቲካ ቅሌቶች ተጠያቂነትን የማያስከትሉ ሳይሆኑ ቀርተው እንዳልሆነ አመልክቷል። መንግሥት የጀመረውን የዴሞክራሲ ምህዳሩን የማስፋት ሂደት አጠናክሮ ከመቀጠል ጎን ለጎን በእንዲህ ዓይነት እኩይ ተግባር ውስጥ የተዘፈቁ  ሃይሎች ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ   አሳስቧል። የተጀመረው የይቅር ባይነት፣ የፍቅር፣ የአንድነትና የመደመር ጉዞ  ቀጣይነት እንዲኖረው ኅብረተሰቡ እስካሁን ያደርግ  የነበረውን  ድጋፍና ትብብር አጠናክሮ  እንዲቀጥል  መንግሥት ጥሪውን  አቅርቧል። ሙሉ መግለጫውን  ከዚህ ያንብቡ፡፡  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም