በኢትዮጵያ ኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 1063 ሆነ

62

ግንቦት 22/2012(ኢዜአ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገ 5034 የላቦራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ 95 ሰዎች ኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሲሆን እስካሁን ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 1063 መሆኑን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።

ትላንት ተጨማሪ 11 ሰዎች ያገገሙ ሲሆን እስካሁን 208 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

ቫይረሱ እንደተገኘባቸው የተረጋገጠ ሰዎች ከ15 እስከ 80 ዓመት የእድሜ ክልል ውስጥ ያሉ 71 ወንድና 24 ሴት ሲሆኑ 94 ኢትዮጵያውያንና 1 የህንድ ዜግነት ያለው  መሆናቸውም ታውቋል።

ቫይረሱ  በምርመራ የተገኘባቸው 56 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ 3 ሰዎች ከትግራይ ክልል፣ 1 ሰው ከአፋር ክልል፣  5 ሰዎች ከአማራ ክልል፣ 22 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣  3 ሰዎች ከሀረሪ ክልል፣  2 ሰዎች  ከድረዳዋ ከተማ አስተዳደር  እንዲሁም  3 ሰዎች ከሶማሌ ክልል መሆናቸው ይፋ ሆኗል። 

ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች መካከል 30 የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያላቸው፣ 4 በበሽታው  ከተያዘ ሰው ጋር  የታወቀ ግንኙነት ያላቸው ሲሆን፤  61 ሰዎች  ደግሞ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነትም ሆነ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ የሌላቸው መሆኑን ሚኒስትሯ በፌስቡክ ገጻቸው ያሰፈሩት መረጃ ያሳያል።  

በሌላ በኩል ትላንት 11 ሰዎች (2 ከትግራይ፤ 9 ከአፈር ክልል) ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን፤ እስካሁን 208 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

በአጠቃላይ ቫይረሱ ተገኝቶባቸው በለይቶ ህክምና ውስጥ ያሉ 845 ሰዎች ናቸው።

በኢትዮጵያ  በቫይረሱ  ምክንያት  የ 8 ሰዎች ህይወት አልፏል።

እስካሁን አጠቃላይ 106, 615 የላቦራቶሪ ምርመራ መከናወኑን ተከናውኗል።

የኮሮና ቫይረስ ስርጭት መጨመርን ከግንዛቤ በማስገባት  ህብረተሰቡ ጥንቃቄዎችን አዘውትሮ እንዲተገብር የጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አሳስበዋል።  

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም