የዘንድሮው አገር አቀፍ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር የፊታችን አርብ ይጀመራል

85

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22/2012 (ኢዜአ) የዘንድሮው አገር አቀፍ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር የፊታችን አርብ ግንቦት 28 በደቡብ ክልል ይጀመራል።

ለችግኝ ተከላው በብዛት ዝግጁ የሆነው  ለምግብነት የሚውሉ የፍራፍሬ ዝርያዎች መሆናቸውም ታውቋል።

ኢትዮጵያ በዚህ ዓመት 5 ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከል የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን አጠናቅቃለች።

ለመርሃ ግብሩ የተዘጋጁ ችግኞችን በሚመለከት ብሄራዊ የአረንጓዴ አሻራ ኮሚቴ አባላት በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን 3 ወረዳዎች ጉብኝት አድርጓል።

ለተከላ ዝግጁ ከሆኑት ችግኞች መካከል የተዳቀሉ የማንጎ ዝርያዎችን ጨምሮ ሌሎች የፍራፍሬ ዝርያዎች መኖራቸውም ታውቋል።

በመሆኑም የዘንድሮው ብሄራዊ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር የፊታችን አርብ በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል በይፋ የሚጀመር መሆኑ ተገልጿል።

እለቱ ዓለም አቀፍ የአካባቢ ጥበቃ ቀን የሚውልበት በመሆኑ ለመርሃ ግብሩ መጀመር ምክንያት መሆኑም ታውቋል።

ለችግኝ ተከላው በብዛት ዝግጁ የተደረጉትም ለምግብነት የሚውሉ የፍራፍሬ ዝርያዎች መሆናቸው ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም