አየር መንገዱ ለሠራተኞቼ ደሞዝ መክፈል አልቻልኩም አለ

66

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 20/2012 (ኢዜአ) የደቡብ አፍሪካ አየር መንገድ ለሠራተኞቹ የግንቦት ወር ደሞዝ መክፈል እንደማይችል ገለጸ።

አየር መንገዱ ለአምስት ሺህ ሠራተኞቹ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት በያዝነው ወር እረፍት ሰጥቷል።

ሠራተኞቹ ደሞዝ የሚያገኙበት አማራጭ ከሥራ አጦች መድህን ፈንድ ሊሆን እንደሚችል የአገሪቱ ሠራተኛ ማኅበር ገልጿል።

ላለፉት 10 ዓመታት ሥራውን ለማከናወን የተቸገረው አየር መንገድ ሠራተኞቹን ሊያሰናብት እንደሚችልም የቢቢሲ ዘገባ ያመለክታል።

ደቡብ አፍሪካ በአፍሪካ አህጉር የሰማይ ትራንስፖርት መሪነት ካላቸው ሦስት አየር መንገዶች አንደኛዋ ሆና ትቆጠራለች።

ከኢትዮጵያና ግብፅ አየር መንገዶች ቀጥሎ አፍሪካን ከሌላው ዓለም ለማገናኘት አየር መንገዱ ያለው ሚናም ''ታላቅ'' የተባለ ነው።

አየር መንገዱ 86 ዓመት ያስቆጠረ ሲሆን፣ 64 አውሮፕላኖች እንዳሉትም መረጃዎች ያመለክታሉ።

ደቡብ አፍሪካ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የተያዙ 24 ሺህ ዜጎች አስመዝግባለች።

ከነዚህም 524ቱ ሞተዋል፣12ሺህ 741ዱ ደግሞ አገግመዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም