ከሊባኖስ 335 ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው ተመለሱ

112

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 20/2012 (ኢዜአ) በሊባኖስ ይኖሩ የነበሩ 335 ኢትዮጵያውያን ዛሬ ወደ አገራቸው ተመለሱ።

የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ከተከሰተ ጀምሮ በተለይ በመካከለኛው ምስራቅ አገሮች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ችግር እየደረሰባቸው መሆኑ ይነገራል።

ችግሩን ለመፍታትም የኢትዮጵያ መንግስት  ዜጎች ወደ አገራቸው እንዲመለሱ እየሰራ ይገኛል።

በመሆኑም በዛሬው እለት ከሊባኖስ ቤይሩት 335 ዜጎች አዲስ አበባ የገቡ ሲሆን፣ በቀጣዮቹ 14 ቀናት በለይቶ ማቆያዎች ይቆያሉ።

ዜጎቹን ወደ አገራቸው የመመለስ ስራ እየተከናወነ ያለው በሦስት መሥሪያ ቤቶች ማለትም በውጭ ጉዳይ፣ በሠራተኛና ማህበራዊ  እንዲሁም በሰላም ሚኒስቴሮች ትብብር መሆኑ ታውቋል።

በቤይሩት በችግር ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን የመመለስ ሥራ የፊታችን ቅዳሜና በቀጣዩ ሳምንት እንደሚቀጥል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም